Thursday, February 23, 2012

ሳያት ልማታዊ ጋዜጠኞቻችንን አትንኪብን(Sayat)

ጋዜጣዊ መግለጫው በሸገር ኤፍኤም ሬዲዮ ፕሮግራም ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም. የታዲያስ አዲስ ፕሮግራም ዋና አዘጋጅ ሰይፉ ፋንታሁን ሳያት ደምሴ በአሜሪካ የነበራትን ኮንሰርት አስመልክቶ ያስተላለፈውን ፕሮግራም አስመልክቶ ነበር፡፡ ሳያት ዘገባውን አስመልክቶ ያቀረበችው ቅሬታ ወደ ፍርድ ቤት ደርሶ ጉዳዩ በሽምግልና እንዲፈታ መስማማታቸውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ተሰባስበዋል፡፡

ከጥንታዊት ኢትዮጵያ ሲተላለፍ እንደመጣው ለሽምግልና ትልቅ ግምት ይሰጣል፡፡ ከባህሉም ከወጉም አንፃር አለመስማማትና ውዝግቡ በሽምግልና ማለቁ የሚያስደስት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሽምግልናውን በማስመልከት በርካታ ጋዜጠኞች መጥራትና መግለጫ መስጠት መፈለጉ ግን ትንሽ ግርምትን ይፈጥራል፡፡

ከሁሉ በላይ የሚያስገርመውና ወዴት ወዴት የሚያሰኘው ግን ሳያት ደምሴ ሚዲያው ላይ የሰነዘረችው መሠረተ ቢስ አስተያየትና ነቀፋ ነው፡፡ በንግግሯ የኢትዮጵያን ሚዲያ በጥቅሉ ጨፍልቃ ‹‹ጥሩ ነገር አታወሩም›› ማለቷ ከምን የመጣ ነው? ‹‹እኛ አገር ስለምናከብረው ሰው እያጣጣላችሁ የምትጽፉት ሁልጊዜም የሚገርመኝ ነገር ማጣጣላችሁ ነው፤ አርአያ የሚሆነን ሰው እያሳጣችሁን ነው፡፡
ሁልጊዜም ከጋዜጠኞች ጋር የምለው በምትጐዱት መልክ ለምንድን ነው የማትጠቅሙት፤ ውሸት ዋሹ ማለት አይደለም፤ የሆነውን ነገር ጻፉ፡፡ ሃያ አራት ሰዓት እንሠራለን፤ እሱ አይጻፍም፡፡ ሁሌ የሚጻፈው አሉታዊ ነገር ነው፤ ተጣሉ ቢሆን ስድሳ ሚዲያ ይመጣ ነበር፡፡ የሚያስጠላ ሥራ ቢሠራ ስለማስጠላቱ ይጻፋል፡፡ ይኼ በጣም ያናድዳል፤›› በማለት ያልተካሔደውን ‹‹ጥናት ውጤቷን›› ገልጻለች፡፡

እንዴት ነው ነገሩ?
ጋዜጦችን፣ራዲዮዎችን፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በምን መነጽር አይታ ነው ከዚህ ድምዳሜ ላይ የደረሰችው? እንዴት ነው ነገሩ?

‹‹ሳያት ምክንያታዊ ሆኖ የመናገር ልማድ ያላት አይመስልም?›› የሚሏት እውነት ነው እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ? በተለያየ ጊዜ ሚዲያ ላይ የመቅረብ ልምድ ኖሮ፣በዚህም ስህተቶች ተፈጥረው፣ከዚህ አወዛጋቢ ነገሮችን ላለመናገርና አላስፈላጊ አስተያየቶችን ከመሰንዘር መቆጠብን እንዴት መማር አይቻልም?  እንዴት ነው ነገሩ?

ሚዲያ ብሎ በጥቅል መጨፍለቅ አለ እንዴ? በተረቱም ‹‹አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት…›› የተባለው አድራሻው ተገኘ እንዴ? እንዴት ነው ነገሩ?

Source : EthiopianReporter

No comments:

Post a Comment