አዳም ለሄዋን(ቅድሚያ ለወንዶች)
"መጀመሪያ ሲፈጥረን
ነበር አንድ ላይ አድርጎ
ሰላሜን ብትነሽኝ ጊዜ
አንድዬ አወጣሽ ፈልቅቆ::
ታዲያ ወጥተሽም አላረፍሽ
በልቤ ውስጥ አድርገሽ ልትገቢ ትሞክሪያለሽ::"
ሄዋን ለአዳም
"መጀመሪያ ሲፈጥረን
ነበር አንድ ላይ አድርጎ
ስትጨቁነኝ ስትበድለኝ
ነጠለና ነፃ አወጣኝ
እኔን ከጎንህ ፈልቅቆ
ታዲያ አንተ መች የዋዛ
አሁንም ትሞክራለህ
ልትጨቁን ልትገዛ::"
ፀጋዬ ኃ. ስላሴ
25-10-2003 ዓ.ም
ፒያሳ( የዳዊት ፀጋዬን "አይዞህ" አንብቤ ሃሳብን ሃሳብ ቢያመጣው ጊዜ"
ሃሳብ ከመጣላችሁ ፃፉት
.
Wednesday, July 20, 2011
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment